Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ችግሮች ያሉ ቢሆንም ዋነኛው ችግር አባባሽ ጉዳይ ነጠላ ትርክት ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ችግሮች ያሉ ቢሆንም ዋነኛው ችግር አባባሽ ጉዳይ ነጠላ ትርክት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛል።

ከሰላምና ጸጥታ ችግሮች ጋር በተያያዘ ለተነሳላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ በኢትዮጵያ በርካታ ችግር መኖሩን ጠቅሰው፤ የችግሩ ዋነኛ አባባሽ ጉዳይ ነጠላ ትርክት መሆኑን አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ችግሮች ያሉ ቢሆንም፤ ዋነኛው ችግር አባባሽ ጉዳይ ነጠላ ትርክት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከፋፋይና እና የሚለያይ ትርክት አገር አፍራሽ መሆኑን መገንዘብ ይገባል ብለዋል።

ታላቅ ትርክት ህዝብ ይሰበስባል፤ ነጠላ ትርክት ደግሞ ህዝብን ይከፋፍላል ሲሉ አስረድተዋል።

እኛ የየትኛውም ሰፈር ጽንፍ የወጣ የዋልታ ረገጥ እሳቤ መጠቀሚያ አይደለንም፤ እኛ የምንከተለው ሀገራዊ እይታ ነው በማለት ገልጸው፤ ችግሮቻችንን የምንመለከትበት ሁኔታ በስሜት እና በሴራ የሚመራ ሊሆን አይገባም ብለዋል።

የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ወደ መፍትሄ መሄድ እንደሚገባ በመግለጽም፤ ኢትዮጵያ የእያንዳንዱ ዜጋ ውጤት ናት፤ በጋራ መኖርና በጋራ መበልጸግም እንችላለን በማለት አስረድተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version