Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከሱዳን ሪፐብሊክ ሉዓላዊ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሱዳን ሪፐብሊክ ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልቡርሃን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም የጋራ በሆኑ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የሱዳን ሪፐብሊክ ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና ልዑካን ቡድናቸው በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ልዑካኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

Exit mobile version