አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሠላም ግንባታ አካታችና የማህበረሰቡን ፍላጎት ያገናዘበ መሆን እንዳለበት ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ አስገነዘቡ፡፡
ፕሬዚዳንቷ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሠላም ግንባታ ኮሚሽን አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ስለ ኮሚሽኑን እንቅስቃሴ ችግሮችና ቀጣይ ሥራ ማብራሪያ ተደርጓል፡፡፡
ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ለጥረቱ አመስግነው፤ ግጭት እንዳይከሰት ካልተደረገ እርስ በእርስ የመዋጋት፣ የመግደል የማውደም አዙሪት ካልተበጠሰ ዘላቂ የሠላም ግንባታ ዘበት ነው ብለዋል።
የሠላም ግንባታ አካታችና የማህበረሰቡን ፍላጎት ያገናዘበ መሆን እንዳለበት ከእራሳቸው ልምድ በመነሳት ማስገንዘባቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

