Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ኢትዮጵያ ገንቢ ሚና ትጫወታለች – አቶ ደመቀ መኮንን

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የደቡብ ሱዳን ልዩ ተወካይ እና በተመድ የደቡብ ሱዳን ተልዕኮ ሀላፊ ኒኮላስ ሮላንድ ሌይቦርን ሃይሶም ጋር ተወያይተዋል፡፡

አቶ ደመቀ ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ፀጥታና ሰላም እንዲረጋገጥ እንዲሁም የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲሆን ያላትን ሚና እየተወጣች መሆኑን ተናግረዋል።

በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለውን የታሪክ፣ የባህል እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መነሻ በማድረግ የቀጠናው ሰላም እንዲረጋገጥና እንዲፀና እየሰራች መሆኑን አስረድተዋል።

በደቡብ ሱዳን የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ ከተደረገ ጀምሮ አንፃራዊ ሰላም በመስፈኑ ኢትዮጵያ ለሰላም የሚደረገውን ጥረት ትደግፋለች ብለዋል።

አቶ ደመቀ በደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ በተቀናቃኞቹ መካከል መተማመን፣ የፖለቲካ ፖርቲዎች፣ ተቋማት፣ ጉረቤት ሀገራት እና ዓለምአቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል ።

ኒኮላስ ሮላንድ ሃይሶም በበኩላቸው ኢትዮጵያ የጎረቤት ሀገራት ሰላም እንዲረጋገጥ ያላት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ተመድ ለሚያደርገው የሰላም ስምምነት አፈፃፀም ኢትዮጵያ ድጋፍ እንድታደርግ ጠይቀዋል።

በሚቀጥለው ዓመት በደቡብ ሱዳን የሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ በአፍሪካ ኀብረት፣ ኢጋድ እና ተመድ በጋራ ለመስራት የኢትዮጵያ ተሳተፎ ጉልህ በመሆኑ እገዛው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ በአካባቢው ሰላም ማስከበር ተልዕኮ የምታደርገውን ድጋፍ ከተመድ ጋር በመሆን ያላትን አጋርነት እና አስተዋጽኦ ልዩ ተወካይ አድናቆታቸውን መግለፃ ቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን በጎረቤት ሀገራት በወቅታዊ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከሱዳን፣ ደቡብ ሱዳንና ከሌሎች በርካታ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ወደ ሀገሪቱ እየገቡ ቢሆንም ከ 1 ሚሊየን በላይ ሰዎች የተሟላ አገልግሎት በመስጠት እያስተናገደች መሆኑን አስረድተዋል።

Exit mobile version