Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኩባ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት የኩባ ምክትል ፕሬዚዳንት ሳልቫዶር ቫልዴዝ ሜሳ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይቸውም÷ ሁለቱ ወገኖች በሕክምና ዘርፍ፣ በቱሪዝም አገልግሎት፣ በትምህርት እና ስኳር ኢንዱስትሪዎች ልማት የተጠናከረ ትብብር በሚኖርበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version