Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኦስትሪያ ቪዬና ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ኦስትሪያ ቪዬና ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በ20ኛው የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) አጠቃላይ ጉባዔ ላይ ለመገኘት ነው ቪዬና የገቡት።
በጉባዔው የክብር እንግድነታቸው የጉባዔውን ቁልፍ ንግግር የሚያቀርቡ መሆኑንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል።
Exit mobile version