አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ20ኛው የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ድርጅት ጉባዔ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ንግግር አድርገዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባቀረቡት ቁልፍ ንግግርም÷ የኢትዮጵያን ያለፉት አምስት ዓመታት የፖሊሲ ለውጥ እና በብዝሃ ዘርፍ እድገት የተደረገ ኢንቨስትመንትን አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም ለአረንጓዴ ልማት እና ንፁህ የኃይል ምንጭ የተሰጠውን ትኩረት አስረድተዋል፡፡
እንዲሁም ለማኅበራዊ ልማት ሥራ የተደረገውን ሁሉ በአፅንዖት መግለጻቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚህም ላይ ተመስርተው ሁሉን አካታች ለሆነ ዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማት ጥሪ አቅርበዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)።