Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የትምህርት ዘርፉን ማነቆዎች መፍትሔ ለመስጠት በሙሉ ተነሳሽነት መስራት ይገባል- ብርሃኑ ነጋ( ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅግጅጋ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 32ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባዔ በዛሬው ዕለት ተጠናቅቋል።

ጉባዔው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በትኩረት ከመከረ በኋላ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ነው የተጠናቀቀው፡፡

በትምህርት ዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታትና ያሉ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል የጉባዔው ተሳታፊዎች ባለ 11 ነጥብ የጋራ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።

ለእነዚህ የጋራ ግንዛቤዎች ተግባራዊነትም ተሳታፊዎች የበኩላቸውን እንደሚወጡ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፥ የጋራ ግንዛቤ የተያዘባቸው የትምህርት ዘርፉ ማነቆዎችን በአጭር ጊዜ መፍትሔ ለመስጠት በሙሉ ተነሳሽነት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ትግበራ ተግዳሮት የሆነውን የመጽሐፍ እጥረት ለመፍታትና የአንድ ለአንድ የመጽሃፍ ተደራሽነትን ለማሳካት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በመጀመሪያው ዙር ታትመው ለክልሎች የተከፋፈሉ መጽሐፍትን ክልሎች በተቻለ ፍጥነት እንዲሰራጩም አሳስበዋል፡፡

በመራኦል ከድር

Exit mobile version