Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኳታር ለኢትዮጵያ የኮሮና መከላከያ የሚውሉ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኳታር መንግስት በኳታር የልማት ፈንድ አማካኝነት ለኮሮናቫይረስ መከላከያ የሚውሉ የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገች።
 
ድጋፍ የተደረጉ የህምክና መሳሪያዎቹ 9 ቶን የሚመዝኑ ሲሆን፥ ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የምታደርገውን ጥረት የሚያግዝ መሆኑንም በኳታር የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
 
የህክምና መሳሪያዎቹ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክን ጨምሮ ለኮቪድ-19 ህክምና መከላከል የሚውሉ ሲሆን፥ በኳታር አየር መንገድ በኩልም ወደ ኢትዮጵያ መላካቸውን ኤምባሲው ገልጿል።
 
የህክምና ቁሳቁሶቹን ወደ ኢትዮጵያ የመላክ መርሃ ግብር ላይም በኳታር የኢትዮጵያ አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ እና የኳታር የልማት ፈንድ ዋና ዳይሬክተር ካሊፋ ቢን ጃሲም አል ካዋሪ ተገኝተዋል።
 
ኳታር በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ለኢትዮጵያ ላደረገችው ድጋፍ ምስጋና ያቀረበው በኳታር የኢትዮጵያ ኤምባሲ፥ በሁለቱ ሀገራት መካከል ጠንካራ የሁለትዮሽ ትስስሮች እየተጠናከሩ መምጣቱን ያሳያል ብሏል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version