Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጅግጅጋ ከተማ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች ዛሬ በድምቀት እየተከበረ ነው።

በዓሉን ለማክበር የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች፣ የብሔር ብሔረሰቦች ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በጂግጂጋ ከተማ ተገኝተዋል።

‘ብዝሃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት’ በሚል መሪ ሀሳብ የሚከበረው በዓሉ ሀገራዊ አንድነትና ሕብረ ብሔራዊነትን ሊያጠናክር በሚያስችል መልኩ እንደሚከበር ተገልጿል።

ከሕዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲከበር በቆየው 18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ ሁነቶች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ይታወቃል።

ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ልምዳቸውን፣ ተሞክሯቸውን፣ ባህላቸውን፣ እሴቶቻቸውን የተለዋወጡባቸው መርሐ ግብሮችም ተዘጋጅተዋል።

የጅግጅጋ ከተማ በዓሉን ለመታደም ለመጡ እንግዶች በተለያዩ ዘርፎች ዝግጅት በማድረግ ቀልጣፋ አገልገሎት እየሰጠች ቆይታለች።

Exit mobile version