አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ ስትራቴጅካዊ አጋርነቷን ለማጠናከር አስተዋጽዖ አለው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለጹ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኳታር 21ኛው የዶሃ ፎረም ላይ ተሳትፈዋል፡፡
ፎረሙ ብሪክስ በባለብዙ ዓለም አቀፍ ሥርዓት ውስጥ እየጨመረ ያለው ተጽዕኖ በሚል መሪ ቃል መካሄዱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
አምባሳደር ምስጋኑ እንዳሉት ፥ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ ስትራቴጅካዊ አጋርነቷን ለማጠናከር አስተዋጽዖ አለው፡፡
ብሪክስ የአፍሪካን የማምረቻ እና የኢንደስትሪያላይዜሽን አቅምን ለማሳየት እና የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠናን በመጨመር ዓለም አቀፍ ንግድን ለማሳደግ ይረዳል ብለዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው አክለው እንደገለጹት፥ ብሪክስ ታዳጊ ሀገራት ባለ ብዙ ወገን ግንኙነታቸውን ለማደስ፣ የግሎባል ደቡብን ህጋዊ ጥቅም ለማንፀባረቅ፣ የበለጠ አሳታፊ እና ፍትሃዊ ለማድረግ ወሳኝ መድረክ ነው።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!