አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ታኅሣስ 7 ቀን 2016 ዓ.ም በአውሮፓ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት እንደሚያካሂድ አስታውቋል፡፡
ኮሚሽኑ በመላው ዓለም ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በበይነ-መረብ ውይይት ማካሄድ መጀመሩንም ነው ያስታወቀው፡፡
የፊታችን እሁድም (በፈረንጆቹ ታኅሣስ 17 ቀን 2023) ከ3፡00 ጀምሮ (3 ፒ ኤም ወይም 15፡00) በአውሮፓ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በበይነ-መረብ ውይይት እንደሚያካሂድ አስታውቋል፡፡
በውይይቱ ላይ ለመሳተፍ ለተመዘገቡት በኢሜይል አማካኝነት የመሰብሰቢያ ሊንኩን እንደሚልክም ነው የገለጸው፡፡
ያልተመዘገቡና በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንም በውይይቱ ለመሳተፍም ይህን ማስፈንጠሪያ https://forms.gle/B5gvhhb3Ecygrjov6 በመጠቀም መመዝገብ እንደሚችሉም ነው ኮሚሽኑ ያስታወቀው፡፡

