Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

መከላከያ በትውልድ ቅብብሎሽ የመጣ ተቋም ነው – ጀኔራል አበባው ታደሰ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መከላከያ ሺህዎች ሞተው ሺህዎች ቆስለው በትውልድ ቅብብሎሽ የመጣ ተቋም ነው ሲሉ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ አስገነዘቡ፡፡

የዓየር ኃይል 88ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አካል የሆነ የፓናል ውይይት ቢሾፍቱ በሚገኘው የዓየር ኃይል መኮንኖች ክበብ እየተካሄደ ነው፡፡

ጀኔራል አበባው የፓናል ውይይቱን ሲያስጀምሩ ባደረጉት ንግግርም÷ መከላከያ ሀገር እንደ ሀገር በትውልድ ቅብብሎሽ እንድትቀጥል የሚያደርግ ተቋም መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

መከላከያን ማንም የሚንደው ተቋም እንዳልሆነም በአጽንኦት በመግለጽ፤ መከላከያ የሚገነባው በሀገር ፍቅር እና በወታደራዊ ሙያ ክኅሎት እንጂ በጊዜያዊ ሆሆታ አለመሆኑንም ነው ያስረዱት፡፡

የዓየር ኃይልን 88ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ስናከብርም ሀገርን በትውልድ ቅብብሎሽ ለማስቀጠል ነው ብለዋል።

ዓየር ኃይል 88ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን የሚያከብረው ከሌሎች የሰራዊቱ ክፍሎች ጋር ተደምሮ ሀገርን ወደፊት ለማስቀጠል መሆኑንም ነው ያስገነዘቡት፡፡

የምስረታ በዓላችንን እራሳችን ክብር ልንሰጠው ይገባል ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version