Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

4ኛው ዙር የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

 

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 4ኛው ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን የሶስትዮሽ ድርድር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ በሐምሌ ወር መጀመሪያ ተገናኝተው የሰጡትን የጋራ መግለጫ ተከትሎ እየተካሄደ ያለ ነው።

ድርድሩ በህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትና አለቃቀቅ ደንቦችና መመሪያዎች ላይ ሥምምነት ለመድረስ ያለመ መሆኑን የኢትዮጵያ ወገን ተደራዳሪዎች ልዑካን መሪ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ባለፉት ዙሮች በተደረጉ ድርድሮች እና የተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተሻለ መግባባት ላይ መድረስ የድርድሩ ትኩረት መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በ2015 በመሪዎች ደረጃ የተፈረመው የመርሆዎች መግለጫ ሥምምነት መሰረት ድርድሩን በፍትሃዊና ምክንያታዊ አጠቃቀም መርህ መሰረት ውጤት ላይ ለመድረስ እንደምትሰራ አስገንዝበዋል፡፡

Exit mobile version