አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት አምስት ዓመታት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ከተመረቱ ምርቶች ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታውቋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶችን ችግር ለመፍታት ያለመ የባለድርሻ አካላት ፎረም እየተካሄደ ነው፡፡
ፎረሙ÷ ባለድርሻ አካላትን በማሰባሰብ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚያመርቱ ኢንቨስተሮች የሚገጥማቸውን ችግር ለመፍታት፣ እልባት የሚሰጥበት እና አቅጣጫ የሚቀመጥበት እንደሆነ ተመላክቷል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እንዳሉት÷ ባለፉት አምስት ዓመታት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ከተመረቱ ምርቶች ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል።
በኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ከ80 ሺህ ለሚልቁ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩንም ነው ያስታወቁት፡፡
ኮርፖሬሽኑ አበረታች ሥራዎችን እያከናወነ ቢሆንም በይበልጥ ውጤታማ ለመሆን የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!