አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ በጅቡቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዲሌይታ መሀመድ ዲሌይታ ከተመራው የልዑካን ቡድን አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ በሁለቱ ወዳጅ ሀገራት ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶች ዙሪያ መክረዋል፡፡
ፕሬዚዳንንት ሣኅለወርቅ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ለ10 ዓመታት ማገልገላቸው ይታወሳል፡፡
ዲሌይታ መሀመድ ዲሌይታም በኢትዮጵያ የጂቡቲ አምባሳደር ሆነው ማገልገላቸውን የፕሬሲዳንት ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!