አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የኮይሻ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን ጎበኙ፡፡
በጉብኝቱ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ፣ የክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ሚኒስትሮች ተገኝተዋል፡፡
በአፍሪካ ደረጃ በግዙፍነቱ ሶስተኛ ደረጃ የሆነውን የኮይሻ ግድብ የንፁሕ የኃይል ማመንጨት ስራ ያለበት ደረጃ አበረታች መሆኑን የሥራ ሃላፊዎቹ ተመልክተዋል፡፡
በጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ በቅርብ ርቀት የሚገኘው የኮይሻ ግድብ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የኢኮኖሚ አቅምና የመልማት ዕድል የሚፈጥር ነው ተብሏል፡፡
በግንባታ ሂደቱም ለበርካቶች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል እየፈጠረ እንደሚገኝ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡