Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመስኖ የተደገፈ የሆርቲካልቸር ሥራ ለማከናወን የተደረገው ጥረት አስደናቂ ውጤቶችን እያሳየ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመስኖ የተደገፈ እና ምርቱ የላቀ የሆርቲካልቸር ሥራ ለማከናወን የተደረገው ጥረት አስደናቂ ውጤቶችን በማሳየት ላይ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የዐሥር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ለፍራፍሬ ምርት እና ሌሎች ዓይነተኛ የዘርፉ ምርቶችን የሚያካትተውን የሆርቲካልቸር ልማት ሥራን ለማስፋፋት ያለመ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በመስኖ የተደገፈ እና ምርቱ የላቀ የሆርቲካልቸር ሥራ ለማከናወን የተደረገው ጥረት አስደናቂ ውጤቶችን በማሳየት ላይ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

የዚህ ውጤት ዋና ማሳያ በፓፓያ ምርት ላይ የታየው ምርታማነት ነው ሲሉም አመላክተዋል፡፡

Exit mobile version