Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አዲሱን የዓባይ ድልድይ ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል እና የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በባሕር ዳር ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን አዲሱን የዓባይ ድልድይ እና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይም የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ፣ የብሔራዊ መረጃ ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል ተመስገን ጥሩነህ፣ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በጉብኝቱ ላይ ተገኝተዋል።

እንዲሁም የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ሕንጻ ግንባታን ለማከናወን የተለየውን ቦታም ጎብኝተዋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር “የመሠረተ ልማት ሥራዎች በፍጥነት መሠራት አለባቸው” ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

በዚህ በጀት ዓመት ለሕንጻ ግንባታው ማስፈፀሚያ 250 ሚሊየን ብር መመደቡንና ፈጥኖም ወደ ግንባታ ሥራ እንዲገባ ይደረጋል ብለዋል።

የካርታ፣ የዲዛይንና ሌሎች ሥራዎችን ፈጥኖ በማጠናቀቅ ግንባታውን ለማስጀመር ርብርብ እያደረጉ መሆናቸውንም አስታውቀዋል፡፡

Exit mobile version