Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የምግብ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ የምናደረገው ጥረት እየተሳካ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምግብ ሉዓላዊነታችንን አስተማማኝ በሆነ መልኩ ለማረጋገጥ የምናደርገው ጥረት እየተሳካ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የዘንድሮ የበጋ መስኖ ስንዴ አምና ከሰራነው በብዙ ይበልጣል፤ እስካሁን የተገኘው ውጤትም እጅግ አመርቂ ነው ብለዋል፡፡

በዓመት ከአንዴ በላይ በማረስ የምግብ ሉዓላዊነታችንን አስተማማኝ በሆነ መልኩ ለማረጋገጥ የምናደርገው ጥረት እየተሳካ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በሁሉም መስክ የምናደርገው ጥረት የብልፅግና መሰረት ይጥላል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በጽሑፋቸው፡፡

Exit mobile version