አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ ዛሬ የተከበረው የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በሰላም መጠናቀቁን አስታውቋል፡፡
በዓሉ በሰላም አንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የኃይማኖት አባቶች እና ለአካባቢው ኅብረተሰብ እንዲሁም ለበዓሉ ከፍተኛ የደኅንነት ጥበቃ ላደረጉ የፀጥታ አካላትም ምስጋና አቅርቧል።
ከበዓሉ ታዳሚዎች የሞባይል እና የተለያዩ ቁሳቁሶችን በመስረቅ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውም ተጠቁሟል፡፡
ግለሰቦቹ በፈፀሙት ወንጀል ጥፈተኛ ሆነው በመገኘታቸው በተቋቋው ጊዜያዊ ችሎት ቀርበው ከስድስት ወር እስከ ሁለት ዓመት ከሦስት ወር በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ እንደተሰወነባቸውም ተመላክቷል፡፡

