Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ዓመታዊ የአምባሳደሮች ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 4 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዲፕሎማሲ ሳምንት አካል የሆነው የአምባሳደሮች ስብሰባ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል።

ስብሰባውን ያስጀመሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ናቸው።

በመድረኩም ሚኒስትሩ የዲፕሎማሲ ስራዎችን አፈጻጸም አንስተዋል።

በእነዚህ ቀናቶችም ከዓመታዊ ስብሰባው ጎን ለጎን የመስክ ጉብኝት እንደሚኖር ተመላክቷል።

በተጨማሪም የሩብ ዓመቱ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያቀርብ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም(ዶ/ር) ገልጸዋል።

የአምባሳደሮች ዓመታዊ ስብሰባ ከዛሬ ጥር 4 ጀምሮ እስከ ጥር 18 እንደሚቀጥል ነው የተገለጸው።

በፍሬህይወት ሰፊው

Exit mobile version