Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሲሪላንካ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ ጉባኤ ጎን ለጎን ከሲሪላንካ ፕሬዚዳንት ራኒል ዊከርሜሲንጌ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ሀገራቱ የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነትን ለማጠናከር እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ትብብራችውን ለማላቅ ያላቸውን ዝግጁነት ማረጋገጣቸውን ጠቁመዋል።15:39

Exit mobile version