Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፖሊስ ጣቢያ የተጠርጣሪ ማቆያዎችን ለማሻሻልና አዲስ ለመገንባት የሚያስችል የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የፖሊስ ጣቢያ የተጠርጣሪ ማቆያዎችን ለማሻሻልና አዲስ ለመገንባት የሚያስችል የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

የድጋፍ ስምምነቱን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ተፈራርመውታል።

የገንዘብ ድጋፉ ከለጋሾች የተገኘ ሲሆን፥ አስር ጣቢያዎችን ለመገንባት እንደሚውል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት የሚተገበር ሲሆን፥ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ታምኖበታል።

በለይኩን ዓለም በትእግስት አብርሃም

Exit mobile version