Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከካናዳው አቻቸው ጀስቲን ትሩዶ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሀገራቱ የሁለትዮሽ እና ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶች ላይ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በቀጣይ ሀገራቱ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እና የጋራ ግቦችን ለማሳካት ቁርጠኛ መሆናቸውንም አንስተዋል፡፡

Exit mobile version