አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው ዶክተር መቅደስ ዳባ ሹመት አጽድቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዶክተር መቅደስ ዳባ የሥራ ልምድ ዘርዝረው ለምክር ቤቱ ባቀረቡት መሰረት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ሹመቱን አፅድቋል፡፡
ዶክተር መቅደስ ዳባ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው የተጣለባቸው ኃላፊነት እንደሚወጡ ቃለ-መሃላ ፈጽመዋል።
ዶክተር መቅደስ ዳባ በማኅጸንና ጽንስ ሕክምና ባደረጉት ምርምርና አስተዋጽዖ በፈረንጆቹ 2021 በሴቶች ዘርፍ የዓለም የጽንስና ማኅፀን ሕክምና ሽልማትን ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡