Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በዓድዋ የነጭ ወረራን ለመከላከል የተደረገው ተጋድሎ ለጥቁር ሕዝቦች የመብት ትግል ፋና ወጊ ነበር- ጁሊየስ ጋርቬይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የታዋቂው ጃማይካዊ ዓለም አቀፍ የጥቁር ሕዝቦች መብት ታጋይና ፓን አፍሪኪኒስት ማርከስ ጋርቬይ ልጅ ጁሊየስ ጋርቬይ (ዶ/ር) የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም በተመለከቱት ነገር እጅግ እንደተገረሙ መናገራቸውን የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በዓድዋ ጦርነት ኢትዮጵያውያን የነጭ ወረራን ለመከላከል በአንድነት ቆመው ያደረጉት ተጋድሎ ለጥቁር ሕዝቦች የመብት ትግል ፋና ወጊ እንደነበርም አውስተዋል፡፡

ይህ ድል መላውን ጥቁር ሕዝብ የሚያኮራ ታሪክ ሲሆን÷ የጦርነቱን ታሪክና ጀግንነት እዚህ በዓድዋ ድል መታሰቢያ በአንድ ማዕከል ተዘጋጅቶ መመልከት መቻል ትልቅ እድል መሆኑንም ገልፀዋል።

የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያውያን አልፎ የመላው ጥቁር ሕዝብ ልብ ውስጥ የታተመ የጋራ አኩሪ ድላችን ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version