Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከኬንያ ጋር አንድ ርዕይ እንዳላቸው ጎረቤቶች በጋራ ለመሥራት ያለን ቁርጠኝነት ተጠናክሯል – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኬንያ ጋር የጋራ አንድ ርዕይ እና እጣፈንታ እንዳላቸው ጎረቤቶች በጋራ ለመሥራት ያለን ቁርጠኝነት ተጠናክሯል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ወንድሜ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ በኬንያ ላደረጉልን ደማቅ አቀባበል አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡

በዛሬው ዕለትም ሰፋ ያሉ ጉዳዮችን ያካተተ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ውይይታቸውም የቆየውን ትስስራችንን ያጠናከረ ብቻ ሳይሆን የወደፊት ቁልፍ የትብብር መስኮችንም የለየ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የጋራ አንድ ርዕይ እና እጣፈንታ እንዳላቸው ጎረቤቶችም በጋራ ለመሥራት ያለን ቁርጠኝነት ተጠናክሯል ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡

Exit mobile version