Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ለሥራ ጉብኝት ጁባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራ ልዑክ ለሥራ ጉብኝት ደቡብ ሱዳን ጁባ ገብቷል።

ልዑኩ የደቡብ ሱዳን መንግሥት ያቀረበለትን ግብዣ ተከትሎ ነው ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ጁባ የገባው፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት ጁባ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የደቡብ ሱዳን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹምና የሀገሪቱ ከፍተኛ የጦር አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከአቀባበሉ በኋላም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ከደቡብ ሱዳን አቻቸው እና ከፍተኛ የጦር መሪዎች ጋር በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በውይይታቸውም ሀገራቱ በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች አሥተማማኝ ፀጥታ እንዲኖር ብሎም በቀጣናው ሠላም ዙሪያ በጋራ ለመሥራት በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ መምከራቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version