Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ አረጋ ከበደ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በአማራ ክልል ወቅታዊ የሰላምና የልማት ሥራዎች ላይ መምከራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በውይይቱ በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ እና የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) ተሳትፈዋል፡፡

Exit mobile version