Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የፌዴራል ተቋማት የብልጽግና ፓርቲ አባላት ማጠቃለያ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ተቋማት የብልጽግና ፓርቲ አባላት ማጠቃለያ ኮንፈረንስ “ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በኮንፈረንሱ ላይ÷ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ፣ በፌዴራል ደረጃ የሚገኙ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የፓርቲው አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ፓርቲው የግማሽ ምርጫ ዘመን አፈፃፀም የሚገመገምበት እና የቀጣይ አቅጣጫዎች የሚቀመጡበት ይህ ኮንፈረንስ÷ በፓርቲው የክልልና ከተማ አሥተዳደሮች መዋቅር ደረጃ ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በተመሳሳይ ኮንፈረንሱ በተለያዩ የፌዴራል ተቋማት ደረጃም ሲካሄድ የቆየ ሲሆን÷ በዛሬው ዕለት የማጠቃለያ ኮንፈረንስ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል ውስጥ የገጠሙትን ተግዳሮቶች ተቋቁሞ ለሕዝቡ የገባውን ቃል እየፈጸመና ስኬቶችን በማስመዝገብ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ፓርቲው በፈተና ውስጥ ድል ማድረግን ያሳየ፣ ፈተናዎች ወደ ዕድል ቀይሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለኢትዮጵያ የተለያየ እውቅና ያስገኘ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

ፓርቲው ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ጉዞውን በድል አጅቦ እየተገበረ እንደሚገኝና ስኬቶችን በማስጠበቅ ለቀጣይ ከፍታ እንደሚሠራ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በብልጽግና ጉዞ ኅብረ-ብሔራዊ ኢትዮጵያን ለመገንባት እንደሚሠራም ነው የተመላከተው፡፡

ኮንፈረንሱ ባለፉት ጊዜያት የተገኙ ስኬቶችን እና መልካም ተሞክሮዎችን ለማስፋት እንደሚረዳ እንዲሁም የገጠሙ ተግዳሮቶችን በማረም ፓርቲው ለሕዝቡ የገባውን ቃል ይበልጥ ተግባራዊ እንዲያደረግ ዕድል እንደሚፈጥርም ተገልጿል፡፡

Exit mobile version