Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮ ሱዳን የባቡር ፕሮጀክት የአዋጭነት ጥናት 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ

ዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአፍሪካ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ለኢትዮ ሱዳን የባቡር ፕሮጀክት የአዋጭነት ጥናት ለኢትዮጵያ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ።
 
1 ሺህ 522 ኪሎ ሜትር የሚረዝመውና አዲስ አበባን ከካርቱም የሚያገናኘው ይህ የባቡር ፕሮጀክት እንዲገነባ በሁለቱ ሀገራት መንግስታት ይሁኝታን ማግኘቱ ይታወሳል።
 
የባቡር ፕሮጀክቱ ከካርቱም አልፎም በቀይ ባህር ላይ ከሚገኘው ፓርት ሱዳን ጋር የሚገናኝ ነው ተብሏል።
 
ባንኩ ያፀደው ድጋፍ ለአዋጭነት ጥናቱ ከሚያስፈልገው 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር 35 በመቶውን የሚሸፍን መሆኑን የሎጄስቲክ አፍሪካ ዘገባ ያመለክታል።
 
ለኢትዮ ሱዳን የባቡር ፕሮጀክት የአዋጭነት ጥናት የሚያስፈልገው ቀሪ ወጪ 2 ሚሊየን ዶላር በኔፓድ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክት ዝግጅት ፋሲሊቲ በድጋፍ መልኩ እንደሚሸፈን ይጠበቃል።

እንዲሁም ኢትዮጵያ እና ሱዳን እያንዳንዳቸው ለአዋጭነት ጥናቱ 100 ሺህ ዶላር ወጪ እንደሚያደርጉ  ተጠቁሟል።

 
ሁለት ዓመታትን የሚፈጀው የአዋጭነት ጥናት የባቡር ፕሮጀክቱን ቴክኒካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ አካባቢያዊ ተስማሚነትን እንዲሁም አማራጭ የፋይንስ ዝግጅትን የሚዳስስ ነው።
 
ባንኩ ኢትዮጵያ እና ሱዳንን ጨምሮ የአፍሪካ ቀንድን የሚያስተሳስሩ ከፍተኛ አቅም ያላቸው መንገዶች አለመኖራቸው በንግድ ፣ ልማት እና ቀጣናዊ ውህደት ላይ ክፍተት መፍጠሩን ነው የገለፀው።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version