Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኮሮና ቫይረስ ሊፈታ የሚችለው በጋራ እርምጃ እና በዓለም አቀፍ ትብብር ብቻ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ስለ ምጣኔ ሀብት ማገገምና ስለ አዲስ የዕድገት አቅጣጫ ባዘጋጀው “ታላቁ ዳግም ማስጀመሪያ” የኦንላይን ስብሰባ ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡

በዚህ ወቅትም የወረርሽኙን ዓለም አቀፋዊ ውስብስብንነት እና ለመላመድ ያለውን ፈተና ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ችግሩ ሊፈታ የሚችለው በጋራ ርምጃዎች እና በዓለም አቀፍ ትብብር ብቻ ነው ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሁኑ ዓለም አቀፋዊ ገጽታ በታሪክ ውስጥ አዲስ አስተሳሰብ ፈጥሮአልም ነው ማለታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የጋራ ፍላጎትን በመወከል የዓዋቂ አስተሳሰብን እና ድፍረትን ሊጠቀም የሚችል የዓለም አቀፍ አመራር ክፍተት እንዳለ ገልፀዋል።

Exit mobile version