አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መጪውን የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ለሚኖሩ አቅመ ደካሞችና በዝቅተኛ ኑሮ ለሚገኙ ወገኖች ማዕድ አጋሩ።
ፕሬዚዳንቷ በዚህ ወቅት በስተላለፉት መልዕክት÷ ድጋፉ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ መደጋገፍ የእለት ተእለት ተግባር መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።
መጪውን የትንሳኤ በዓል ከአቅመ ደካማ ወገኖች ጋር አብሮ ማሳለፍ ይገባል ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡
የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክፍሉ ገዛኸኝ÷ ፕሬዚዳንቷ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበው መንግስት ለነዋሪዎች ተጠቃሚነት የተለያዩ ድጋፎች እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸው ነዋሪዎች ፕሬዚዳንቷ የትንሳኤ በዓልን ተደስተው እንዲውሉ ላደረጉላቸው ድጋፍ አመስግነዋል።