Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኦሮሞ ሕዝብ ያገኘውን ለውጥ በማስቀጠል ሠላሙን መጠበቅ አለበት- ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኦሮሞ ሕዝብ ያገኘውን ለውጥ በማስቀጠል ሠላሙን መጠበቅና አንድነቱን ማጽናት እንዳለበት አስገነዘቡ፡፡

ከአራቱም የወለጋ ዞኖች የተውጣጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ሀገራዊ ለውጡን የሚደግፍ ሰልፍ በነቀምቴ ከተማ ወለጋ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሕዝባዊ የድጋፍ መድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ሠላም፣ አንድነትና የኢኮኖሚ ነጻነትን ማረጋገጥ ላይ ያተኮሩ ሐሳቦችን አንስተዋል::

የኦሮሞ ሕዝብ ያገኘውን ለውጥ በማስቀጠል ሠላሙን መጠበቅና አንድነቱን ማጽናት እንዳለበትም ገልጸዋል፡፡

በአካባቢው የተገኘውን ሠላም ኅብረተሠቡ ማስቀጠል እንደሚኖርበት ማስገንዘባቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version