Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሠራተኞችና ድርጅቶች ለ #ጽዱኢትዮጵያ ዲጂታል ቴሌቶን 64 ሚሊየን ብር ለገሱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሠራተኞችና ድርጅቶች ለ #ጽዱኢትዮጵያ ዲጂታል ቴሌቶን 64 ሚሊየን ብር ለገሱ፡፡

#ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ በአንድ ጀምበር 50 ሚሊየን ብር የማሰባሰብ የዲጂታል ቴሌቶን እየተካሄደ ነው፡፡

በዚሁ መሠረት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሠራተኞች 14 ሚሊየን እንዲሁም በሥሩ ያሉ ድርጅቶች 50 ሚሊየን ብር ለግሰዋል፡፡

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጀማል አሕመድ ለ #ጽዱኢትዮጵያ በግላቸው 1 ሚሊየን ብር ለግሰዋል፡፡

መላው ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248፣ በብሔራዊ ባንክ የዶላር አካውንት 0101211300016 እና በስዊፍት ኮድ NBETETAA የ“ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ንቅናቄ የቻሉትን አስተዋጽ በማድረግ ንቅናቄውን እንዲቀላቀሉ ተጠይቀዋል፡፡

Exit mobile version