አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሣይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ላይ ትኩረቱን ያደረገው “ስትራይድ ኢትዮጵያ 2024” አውደ ርዕይ በሳይንስ ሙዚዬም ተከፈተ።
በአውደ ርዕዩ መክፈቻ ላይ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር ዴዔታ ባይሳ በዳዳ(ዶ/ር) ጨምሮ የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
በአውደ ርዕዩ የተለያዩ የፈጠራ ውጤቶች እና የቴክኖሎጂ ሥራዎች ለዕይታ ቀርበዋል።
ዛሬ በይፋ በሳይንስ ሙዚዬም የተከፈተው አውደ ርዕይ “ሣይንስ በር ይከፍታል ፤ ቴክኖሎጂ ያስተሳስራል ፤ ፈጠራ ወደ ፊት ያራምዳል” በሚል መሪ ሃሳብ እስከ መጪው ግንቦት 18 ቀን እንደሚቆይ ተመላክቷል።
በወንድሙ አዱኛ

