አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢራኑ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡
ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በኢትዮጵያ ሕዝብ፣ መንግስትና በራሳቸው ስም በደረሰው አሰቃቂ የሄሊኮፕተር አደጋ ሕይወታቸውን ላጡት የኢራን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሚር አብዱላሂ የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡
ለፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲና አሚር አብዱላሂ ቤተሰቦች እንዲሁም ለኢራን ሕዝብና መንግስትም መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

