Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ እና ሲንጋፖር ግንኙነታቸውን በይልጥ ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ሲንጋፖር የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ለማጠናከር እና አዳዲስ የትብብር መስኮችን ለማጠናከር መስማማታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በዛሬው ዕለት ከሲንጋፖር ፕሬዚዳንት ታርማን ሽሙጋርተናም ጋር ተወያይተናል ብለዋል።

መሪዎቹ በኢስታና ተገናኝተው ባደረጉት ውይይትም በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ሐሳብ መለዋወጣቸውን እና በዚህም ደስታ እንደተሰማቸውም ጠቅሰዋል፡

የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ለማጠናከር እና አዳዲስ የትብብር መስኮችን ለማጠናከር ተስማምተናልም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

Exit mobile version