አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሪፐብሊካን ጋርድ የጥበቃ አባላት ጋር በመሆን ችግኝ ተከሉ፡፡
የሪፐብሊካን ጋርድ የጥበቃ አባላቱ ሃገርን ከመጠበቅ ጎን ለጎን በአከባቢ ጥበቃ ላይ የድርሻቸውን እንደሚወጡ አስታውቀዋል፡፡
የኢፌዴሪ ሃገር መከላከያ ሰራዊት እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ህዝባዊነቱን ለማጠናከር በልማት ስራዎች ተሳትፎውን እንዲሚቀጥል ተገልጿል፡፡
ችግኙን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ፊት ለፊት ነው የተከሉት፡፡
በአላዛር ታደለ

