አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የማላዊ ምክትል ፕሬዚዳንት ሳውሎስ ቺሊማን ጨምሮ የዘጠኝ ሰዎችን ሕይወት በቀጠፈው አሰቃቂ የአውሮፕላን አደጋ የተሰማትን ጥልቅ ሐዘን ገለጸች፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው የሐዘን መግለጫ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ለማላዊ መንግሥት እና ሕዝብ የተሰማውን ሐዘን በመግለጽ መጽናናትን ተመኝቷል፡፡
በዚህ የሐዘን ወቅት የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ ከማላዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና ሕዝብ ጎን መሆናቸውንም ሚኒስቴሩ አረጋግጧል፡፡
የማላዊ መከላከያ ኃይል አውሮፕላን ከትናንትና በስቲያ የሀገሪቱን ምክትል ፕሬዚዳንት ሳውሎስ ቺሊማን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ ሳለ ከራዳር ውጭ መሆኑን ተከትሎ ባጋጠመው የመከስከስ አደጋ ሁሉም ተሳፋሪዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ማሳወቃቸው ይታወሳል፡፡