Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ቆይታቸውን ያጠናቀቁትን የዩኒዶ የኢትዮጵያ ተወካይን አሰናበቱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቆይታቸውን ያጠናቀቁትን የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) የኢትዮጵያ ተወካይ ካላብሮ አውሬሊያ ፓትሪዚያን አሰናበቱ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ተወካይዋ የኢትዮጵያ እውነተኛ ወዳጅ እንደነበሩ ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቅ በመረዳት ለሀገሪቱ ልማት በቁርጠኝነት መሥራታቸውን ገልጸው፤ በቀጣይ የሥራ ሕይወታቸው የተቃና እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

Exit mobile version