Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአቶ አደም ፋራህ የተመራ ልዑክ ጅቡቲ ገባ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ ልዑክ ጅቡቲ ገብቷል።

ልዑኩ ጅቡቲ የገባው በሀገሪቱ በ47ኛው የነጻነት ቀን ላይ ለመታደብ መሆኑን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመልክቷል።

Exit mobile version