Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠ/ሚ ዐቢይ በኢንተርኔት በመታገዝ በተካሄደው የቻይና-አፍሪካ ጉባኤ ተሳተፉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢንተርኔት በመታገዝ በተካሄደው የቻይና-አፍሪካ ጉባኤ ተሳተፉ።

ጉባኤው ኮቪድ19ን ለመግታት በአንድነት የመቆም አስፈላጊነት ላይ ያተኮረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ለመተንበይ የሚያዳግት ጊዜ በአፍሪካ ሀገራት እና በቻይና መካከል የታየው በአንድነት መቆም ዓይነተኛ እሴት መሆኑን አንስተዋል።

በቻይና-አፍሪካ የትብብር ፎረም ወቅት ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ያነሷቸውን ስምንት ዐበይት እንቅስቃሴዎች ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጤና አገልግሎት ቅድሚያና ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

በፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ሰብሳቢነት የተካሄደው ውይይት በቻይና፣ የአፍሪካ ኅብረት ሰብሳቢ በሆነችው ደቡብ አፍሪካ እና ከቻይና-አፍሪካ ትብብር ፎረም ሰብሳቢዎች አንዷ በሆነችው ሴኔጋል ሀሳብ አመንጭነት የተከናወነ መሆኑ ተጠቁሟል።

የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ የተመድ ዋና ጸሐፊ እንዲሁም የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር በጉባኤው ተሳትፈዋል።

Exit mobile version