Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ ደስታ ሌዳሞ የዘንድሮውን ክልል አቀፍ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ የዘንድሮውን ክልል አቀፍ የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ- ግብር በሐዋሳ ዙሪያ ወረዳ ኡምቡሌ ዋጮ ቀበሌ በይፋ አስጀመሩ።

የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር የሚከናወነው “የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ ሐሳብ ነው፡፡

በክልሉ በዘንድሮ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ለምግብነትና ለእንስሳት መኖነት የሚያገለግሉ ተክሎችን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እንደሚተከሉ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የችግኝ ተከላው ከ29 ሺህ ሄክታር በሚልቅ መሬት ላይ እንደሚካሄድም ነው የተመላከተው፡፡

Exit mobile version