Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ከተለያዩ ሀገራት ጋር በሚኖር ፓርላሜንታዊ ግንኙነት ዙሪያ መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ከተለያዩ ሀገራት ጋር በሚኖር ፓርላሜንታዊ የሁለትዮሽ ግንኙነቶች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

በአፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር የተመራ ልዑክ በሩሲያ ሴይንት ፒተርስበርግ ከተማ ለብሪክስ አባል ሀገራት በተዘጋጀው ፓርላሜንታዊ ዓመታዊ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡

ከጉባዔው ጎን ለጎንም አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ከሩሲያ፣ አዘርባጃን እና ኢራን የፓርላማ ልዑካን ቡድኖች ጋር በሁለትዮሸ ግንኙነት ዙሪያ መክረዋል፡፡

ከሩሲያ ካውንስል አፈ-ጉባዔ ቫሌንቲኖ ኢቫኖቭና ማትቪዮንኮ ጋር በተደረገው ውይይት÷ የሁለቱን ሀገራት አጠቃላይ ግንኙነት በይበልጥ ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑ፤ ፓርላሜንታዊ ግንኙነቶችን ለማጠናከር ደግሞ ተቀራርቦ መሥራት እንደሚገባ ተነስቷል፡፡

በተጨማሪም የሁለቱን ሀገራት ፓርላሜንታዊ ግንኙነቶች ለማጠናከር የልምድ ልውውጦች፣ ሥልጠና እና ሌሎች ድጋፎችን ማጠናከር እንደሚገባ የተገለጸ ሲሆን ወደ ተግባር ለመግባት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

አፈ-ጉባዔ አገኘሁ በበኩላቸው ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን ሁለንተናዊ ለውጥ ያብራሩ ሲሆን÷ ቀጣይ ከሩሲያ ፓርላሜንት ካውንስል ጋር የሚደረገው ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

Exit mobile version