አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመቻልን 80ኛ ዓመት ምሥረታ አስመልክቶ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደውን ጨዋታ የዑጋንዳው ኪታራ ቡድን መቻልን 2 ለ 0 ረትቷል፡፡
የመቻል ስፖርት ክለብ 80ኛ ዓመት ምስረታን አስመልክቶ ቀደም ብለው በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች÷ የአርቲስቶች ቡድን የመቻል የቀድሞ ተጫዋቾችን 3 ለ 0 እንዲሁም የባለስልጣናት ቡድን ባለሃብቶችን 2 ለ 1 አሸንፈዋል፡፡
ፖርቹጋላዊው ሉዊስ ናኒ እና ናይጄሪያዊው ኑዋንኮ ካኑም በስታዲየም ተገኝተው ጨዋታውን ተከታትለዋል፡፡