እነዚህ ጥረቶች ለዘላቂነት እና ለአካባቢ ጥበቃ ቅድሚያ በመስጠት ቱሪዝምን ለማሳደግ፣ ስራ ለመፍጠር እና በዙሪያው የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎችን የኑሮ ደረጃ ለማሳደግ ያለሙ ናቸው።
ቱሪዝም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ገቢ በማስገኘት እና በሚሊየን የሚቆጠሩ ሥራዎችን በመደገፍ በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
ለጠቅላላ ሀገራዊ ምርት (GDP) በሚያደርገው ቀጥተኛ አስተዋፅኦም በጎ የሆነው ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖው በጉልህ ይታያል።
በሀገራችን ኢትዮጵያም ቱሪዝም መንግስት ላስጀመረው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም የማዕዘን ድንጋይ ሲሆን ከአምስቱ ቁልፍ ምሰሶዎች አንዱ ነው።
እንደ “ገበታ ለሀገር” ያሉ ሥራዎች የቱሪዝም ዘርፉን ለማዳበር፣ ብዙ ጎብኝዎችን ለመሳብ፣ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማነቃቃት፣ የስራ እድሎችን ለመፍጠር፤ መዳረሻዎችን ለማልማት እና ለማሻሻል ታልመው በሥራ ላይ በመዋል ላይ ይገኛሉ።
የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ምረቃ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አራት ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መዳረሻዎችን በ “ገበታ ለሀገር” ውጥን ስር ለማልማት ያሳዩት ቁርጠኝነት ተጨማሪ ማሳያ ሲሆን በ2012 ቃል በገቡት መሰረት ገንብተው ማስረከባቸውንም ያመላክታል።
በአሁኑ ወቅት ደግሞ ርዕያቸው ተስፋፍቶ በግንባታ ላይ ያሉ ሰባት ተጨማሪ መዳረሻዎችን ለማልማት ያቀደ “ገበታ ለትውልድ” የተሰኘ አዲስ ፕሮጀክትም አስጀምረዋል።›› – የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት