አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፌ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራል መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች አጽናኑ፡፡
በወረዳው ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ ከትናንት በስቲያ በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ የተከሰተው የመሬት መንሸራተት በሰውና በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ማስከተሉ ይታወሳል።
ይህን ተከትሎም አፈ-ጉባዔ ታገሰን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በቦታው ተገኝተው ማጽናናታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የክልሉ መንግሥትና የአካባቢው ነዋሪዎች በአሁኑ ወቅት የነፍስ አድንና ተጨማሪ አደጋ እንይከሰት ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን በርብርብ እያከናወኑ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሚደረጉ የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራዎችም በቅንጅት እየተከናወኑ ነው፡፡