Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት እና በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የሚንቀሳቀሱ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ፡፡

ከችግኝ ተከላው በተጨማሪ የቤት እድሳት መርሐ-ግብር ማስጀመራቸውን የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ሞገስ ባልቻ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም “ያለችን ሀገር አንድ መሆኗን በመገንዘብ በጋራ ዐሻራችንን እናኑር፤ እናልማት፤ እናበልጽጋት” ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Exit mobile version